ይህም ሳናኤ ታካኢቺ ባለፈው ጥቅምት ወር ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተመረጡ በኋላ የተፈጸመ የመጀመሪያው የሞት ቅጣት ነው።
በቶኪዮ የሚገኘው ኪዮዶ ኒውስ እንደዘገበው፤ፍርድ ቤቱ የ58 ዓመቱ ሱናኦ ታካሚን የሞት ቅጣት በ2016 ያጸደቀው ሲሆን፤ ግለሰቡ በሞት በመቀጣቱ ከሰኔ 2025 ወዲህ በጃፓን የሞት ቅጣት የተፈጸመበት ‹‹የመጀመሪያው›› ሰው ሆኗል።
ግለሰቡ በሐምሌ 5 ቀን 2009 ‹‹ፓቺንኮ ፓርለር›› ተብሎ በሚጠራ መዝናኛ ስፍራ ውስጥ ነዳጅ በማፍሰስ ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ መገኘቱን ዘገባው አክሎ ገልጿል። በዚህ ጥቃት ቢያንስ 10 ሌሎች ሰዎች ቆስለዋል።
የፍትህ ሚኒስትሩ ከቅጣቱ አፈጻጸም በኋላ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፤‹‹የሞት ቅጣቱ እንዲፈጸም ያዘዝኩት በጥንቃቄ ካሰብኩበት በኋላ ነው››ብለዋል።
በቶኪዮ አቅራቢያ በሚገኘው ካናጋዋ ግዛት ዘጠኝ ሰዎችን በመግደል፣ አካላቸውን በመቆራረጥ እና በማከማቸት ጥፋተኛ ተብሎ በሰኔ 2025 የሞት ቅጣት የተፈጸመበት የ34 ዓመቱ ታካሂሮ ሺራኢሺ በጃፓን የመጨረሻው የሞት ቅጣት የተፈረደበት ግለሰብ እንደነበር ተጠቅሷል።
በ2024 አንድ የጃፓን ፍርድ ቤት ኢዋኦ ሃካማታ የተባሉትን ግለሰብ ከ40 ዓመታት በላይ በሞት ፍርድ ጥላ ስር ከቆዩ በኋላ ከወንጀል ነፃ ማድረጉ የሚታወስ ነው።
እስከዳር ግርማ
ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም
