ቴምር ፕሮፐርቲስ 75 ለሚጠጉ የደን ጠባቂ ሬንጀሮችና “Plogging Ethiopia” የተባለውን ተቋም በመመስረት ላለፉት 6 ዓመታት በበጎ ፈቃደኝነት የወዳደቁ ፕላስቲኮችንና ቆሻሻዎችን በመሰብሰብ ለአካባቢ ጥበቃ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱት ለፕሮፌሰር ፍሬው ከፍያለው ልዩ ዕውቅናና ስጦታ ሰጥቷል።
ቴምር ፕሮፐርቲስ ለአካባቢ ጥበቃ የማይተካ አስተዋፅኦ ለሚያበረክቱ የጉለሌ እፅዋት ማዕከል ሬንጀሮች ዕውቅናና ስጦታ ሰጥቷል።
የጉለሌ እዕዋት ማዕከል እዕዋትን በመሰብሰብ፤ በማሰራጨትና ወደ ተፈጥሯዊ መኖሪያቸው እንዲመለሱ በሚደረጉ የምርምርና የጥበቃ ሥራዎች ወሳኝ ሚና እንደሚሰጥ ተነግሯል።
በማዕከሉ ሥር የሚገኙ ሬንጀሮችም የደን ሀብትን፣ ብዝሃ ሕይወትን የሥነ-ምህዳር ሚዛንን ለመጠበቅ በየዕለቱ ከፍተኛ ኃላፊነት እንደሚወጡ ተገልጿል፡፡
ዕውቅናዉ ለአቶ ፍሬው የተሰጠ ግለሰባዊ ሽልማት ብቻ ሳይሆን፤ ለተፈጥሮና ለአካባቢ ጥቢቃ በተግባር ለሚተጉ ሁሉ የሚሰጥ አድናቆት፤ ማበረታቻና የአካባቢ ጥቢቃ ተሳትፎን ለማጠናከር የታለመ መልዕከት ነው ተብሏል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ነሐሴ 21/2018 ዓ
