ውድ የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን ባለፉት ሁለት ተከታታይ ቀናትበቅድመ ክፍያ (Prepaid card) አገልግሎት ሲስተማችን ላይ አጋጥሞ የነበረው የቴክኒክ ብልሽት ሙሉ በሙሉ ተቀርፎ፣ አሁን ላይ መደበኛ የካርድ መሙላት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን እንገልጻለን።
በተፈጠረው መስተጓጎል ወቅት ላሳያችሁት ትዕግሥትና መረዳት ከልብ እያመሰገንን፤ አሁኑኑ በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን በመገኘት አገልግሎቱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም
