ውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል፥ “ጳጉሜን ለጤና” በሚል መሪ ቃል ላለፉት 16 ዓመታት ሲያካሂድ የቆየውን ነፃ የሕክምና ምርመራ እና የበጎ አድራጎት መርሃ ግብር ዘንድሮም ለ17ኛ ጊዜ እንደሚያካሒድ አሳውቋል::
ዘመቻው በአቅም ማነስ ምክንያት የሕክምና ምርመራ ወጪ መሸፈን ለማይችሉ እና በሐኪም የታዘዘ የምርመራ ወረቀት በእጃቸው ለሚገኝ ዜጎች ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፥ ከነሐሴ 28 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለ5 ተከታታይ ቀናት ይቆያል።
በዚህም መሰረት የCT Scan፣ MRI፣ X-ray እና Ultrasound (3D፣ 4D) ህክምና ምርመራዎች የልብእናየልብ ምርመራ (Echo) እና ECG ምርመራዎች በነፃ ይሰጣሉ።
በተጨማሪም በ ISO የተረጋገጠ የላቦራቶሪ ምርመራዎች በተከታታይ ለ5 ቀናት ይሰጣሉ።
ከነፃ የሕክምና ምርመራዎቹ በተጨማሪ፥የውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል የማህበረሰብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ አምስቱን የጳጉሜ ቀናት መሰረት ያደረጉ ልዩ ልዩ የበጎ አድራጎት ተግባራትን ለማከናወን ማቀዱም ታውቋል።
የዘንድሮ የ“ጳጉሜን ለጤና” 17ኛ ዓመት ክብረ በዓል የሕክምና አገልግሎትን “ከአባቶች ክብርና ቡራኬ” ጋር በማስተሳሰር የሚታሰብ ይሆናል ተብሏል።
ውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ለ24 ሰዓታት ክፍት በመሆን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
የዚህ ነፃ የሕክምና ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን የሚፈልጉ የሐኪም ትዕዛዝ በእጃቸው የሚገኝ ዜጎች፥ከነሐሴ 28 እስከጳጉሜ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ቀናት በአጭር ስልክ ቁጥር 9888 ወይም በ0940-040404 / 0940-050505 በመደወል መመዝገብ እንደሚችሉ ማዕከሉ ገልጿል።
ሀና ሰይፉ
ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም
