በአዲስ አበባ አንድ ሰው ወንዝ ውስጥ ገብቶ ህይወቱ አለፈ፡፡

አደጋው የደረሰው በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ሊዩ ቦታው ማሞ ወንዝ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ነው ፡፡

በግምት እድሜው 29 አመት የሆነው ወጣት ወንዝ ውስጥ ገብቶ ህይወቱ ወዲያው እንዳለፈ ነው የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም የተናገረው፡፡

ይሁንና ወጣቱ ለምን ወደ ወንዙ ውስጥ እንደገባ እስካሁን አልታወቀም ተብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም ቅዳሜ እና እሁድ በከተማዋ ሁለት የእሳት አደጋዎች ተከስተው እንደነበረም ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

የመጀመርያው የእሳት አደጋ የደረሰው በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት ሲሆን በአምስት መኖርያ ቤቶች የደረሰ የእሳት አደጋ ነው፡፡

በዚህ አደጋ ምክንያት 240 ሺህ ብር የሚጠጋ ንብረት የወደመ ሲሆን 20 ሚሊየን የሚገመት ንብረት ደግሞ ማዳን ተችሏል፡፡

ሌላኛው አደጋ የደረሰው ደግሞ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ አካባቢ በፎቶ ቤት የደረሰ የእሳት አደጋ ሲሆን 3 ሺህ ብር የሚጠጋ ንብረት መውደሙን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

እንደዚሁም 10 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ከውድመት መታደጉን የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ አቶ ጉልላት ጌታነህ ለኤትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 22 ቀን 2012

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *