ፓኪስታን በሰነዘረችው የአየር ጥቃት በአፍጋኒስታን የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ

በሰሜን ምስራቅ አፍጋኒስታን ኩናር ግዛት በፓኪስታን በተሰነዘረ የአየር ድብደባ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሶስት ሰዎች መገደላቸውን እና አራት መቁሰላቸውን የአፍጋኒስታን ባለስልጣናት ገልጸዋል።

ጥቃቱ ኑርጋል የተባለውን ወረዳ መምታቱ ታውቋል። በተጨማሪም በፓክቲካ ግዛት ተመሳሳይ ጥቃት ቢሰነዘርም የሰው ህይወት እንዳልጠፋ ተገልጿል።

ፓኪስታን ስለ ጥቃቱ ወዲያውኑ የሰጠችው አስተያየት ባይኖርም፤ይህ ክስተት ለሶስት ወራት ሰፍኖ የነበረውን አንጻራዊ ሰላም በማቋረጥ በሁለቱ ጎረቤት ሀገራት መካከል ያለውን ውጥረት ዳግም ሊቀሰቅስ እንደሚችል ተሰግቷል።

የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሻከረ ሲሆን፤ ኢስላማባድ ካቡልን ‹‹ድንበር ተሻጋሪ ጥቃት የሚያሰነዝሩ ታጣቂዎችን ታስጠጋለች›› ስትል ትከሳለች፤ ታሊባን ግን ውንጀላውን ያስተባብላል።

የአየር ጥቃቱ የተፈጸመው ታሊባን መስጊድ ላይ 21 ሰዎችን የገደለ ጥቃት መፈጸሙን ካስታወቀ እና ፓኪስታን በአፍጋኒስታን ውስጥ ያሉ ታጣቂዎችን እንደምትመታ ካስጠነቀቀች ከጥቂት ቀናት በኋላ ነው።

ሳራ ዮሐንስ

መስከረም 11/2019

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *