የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 59ኛ መደበኛ ስብሰባ በሁለት ደንቦች እና በዓራት ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።

ምክር ቤቱ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ በሙሉ ድምፅ የወሰናቸው ረቂቅ አዋጆች፡-ሀገራዊ ምርጫን ተከትሎ የፌዴራል አስፈጻሚ አካላትን በአዲስ መልክ ለማቋቋም የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ፣የሀገሪቱን የዳታ ደህንነት ለማረጋገጥ እና የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን የተዘጋጀውን የብሔራዊ ዳታ አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ፣ለኃይል ሴክተር ማሻሻያ ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር የተገኘውን የ145 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኤስ.ዲ.አር (SDR) የብድር ስምምነት ማጽደቂያ፣እንዲሁም የመከላከያ ሠራዊቱን ህገ-መንግስታዊ ተልዕኮ ለማጠናከር የቀረበውን የመከላከያ ሠራዊት ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ናቸው።

በሌላ በኩል ምክር ቤቱ፤ ግልጽነትና አስተዳደራዊ ቅልጥፍናን የሚያረጋግጠውን የፌዴራል ገቢ ግብር ማሻሻያ ደንብ እና በመሰረታዊ አቅርቦቶች ላይ ያለውን የዋጋ ጫና የሚቀንሰውን የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ማሻሻያ ደንብ ላይ ተወያይቶ በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውሉ በሙሉ ድምፅ ወስኗል።

መስከረም 18/2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *