“ስልጣን የግል ጥቅም ማካበቻ እንዳይሆን እንሰራለን” — ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደሩን መንግሥት ምስረታ እና የ4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤውን በዓድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኘው የምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል።

በዚሁ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ ስልጣን የግል ጥቅም ማካበቻ እንዳይሆን በጽናት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ከንቲባዋ በንግግራቸው ከተማዋን በድጋሚ እንድመራ ለተጣለብኝ እድል እና ኃላፊነት የከተማውን ህዝብ ከልብ አመሰግናለሁ ያሉ ሲሆን፣ በ7ኛው ዙር ምርጫ የተመዘገበው ውጤትም ህብረብሔራዊ ብዙሃንነትን በግልጽ ያሳየንበት ነው ብለዋል።

አያይዘውም ሙስናን የሚጠየፍና የሚታገል የከተማ ነዋሪ እንዲሁም የመንግሥት ሰራተኛ ለመፍጠር በቅንጅት እንደሚሰራ የገለጹት ከንቲባዋ፣ በቀጣይ የሥራ ዘመናት የሕዝቡን መሠረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

በተለይም ህብረተሰቡን እየፈተነ የሚገኘውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠርና የኑሮ ውድነትን ለማቃለል በቀጣይ ጊዜያት በበለጠ ትጋት እንደሚሰራ የጠቆሙ ሲሆን፣ የንጹሕ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና የመኖሪያ ቤት ተደራሽነትን ለማሳደግ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

ለዓለም አሰፋ
መስከረም 20/2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *