ገዳ ባንክ «ገዳ ዲጂታል ኦንቦርዲንግ » የተሰኘ አዲስ የዲጂታል ምዝገባ ቴክኖሎጂ ይፋ አደረገ፡፡

ገዳ ባንክ ከደንበኞች ጋር ያለውን ቁርኝት ለማጠናከር እና የባንክ አገልግሎቶችን ከቀጠሮና ከቢሮ ውጭ ለማድረግ የሚያስችል «ገዳ ዲጂታል ኦንቦርዲንግ» የተሰኘ አዲስ የዲጂታል ምዝገባ ቴክኖሎጂ አስታውቋል።

ይህ አዲስ ዘመናዊ ፕሮዳክት ሙሉ በሙሉ አውቶማቲክ በመሆኑ፣ ደንበኞች ባንክ በአካል በመገኘት ወይም ቅርንጫፍ በመጎብኘት ጊዜ ሳያባክኑ በማንኛውም ሰዓት እና ቦታ ያለ ምንም እንከን የባንክ አገልግሎቶችን ማግኘት እንዲችሉ ያስችላል ተብሏል።

​ፕሮዳክቱ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የደንበኞችን ማንነት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚያረጋግጥ ሲሆን፣ ግለሰቡ በህይወት መኖሩን የሚያረጋግጥ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሂደቱን ደህንነቱ የተጠበቀ እና ከማጭበርበር የጸዳ እንደሚያደርገው ተጠቅሷል።

በተጨማሪም የደህንነት ማረጋገጫ ኮዶች በቀጥታ በጽሁፍ መልእክት እና በኢሜይል የሚላኩበት ባለብዙ ደረጃ ማረጋገጫ ስርዓት ተካቶበታል።

ይህ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አዲስ መፍትሄ የባንኩን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ከፍ ከማድረጉም በላይ፣ የደንበኞችን ተለዋዋጭ ፍላጎቶች ምላሽ የሚሰጥ መሆኑን ባንኩ አስታውቋል።

ሐመረ ፍሬው
መስከረም 20/2019 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *