የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዕለታዊ መግለጫ በመስጠት ላይ ሳሉ ነው ዋይት ሐውስ አካባቢ በተሰማ ተኩስ ምክንያት ጋዜጣዊ መግለጫውን አቋርጠው ከጠባቂዎቻቸው ጋር መውጣታቸው የተነገረው ።
የፕሬዝዳንቱ የልዩ ጥበቃ መኮንን ድንገት ጋዜጣዊ መግለጫው እየተሰጠ ነበር አቋርጦ ወደ መድረክ የወጣው፡፡
ከዚያም በጆሯቸው አንድ ነገር ሹክ ካላቸው በኃላ ዶናልድ ትራምፕን ይዞ ከክፍሉ ውሰጥ እንዲወጡ አድርጓል ብሏል ሲ ኤን ኤን ።
ከደቂቃዎች በኋላ ወደ ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል የተመለሱት ትራምፕ የተፈጠረው ችግር በአስተማማኝ ሁኔታ በቁጥጥር ሥር ውሏል ብለዋል ሲጠብቋው ለነበሩት ጋዜጠኞች።
ሲመለሱ ምን እንደተከሰተ የተጠየቁት ትራምፕ የልዩ ጥበቃ አባል አንድን ተጠርጣሪ ተኩሶ እንደመታውና ወደ ሆስፒታል ተወስዷል ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በልዩ ጥበቃ ዘብ ታጅበው ዙር የተደረጉት ለዘጠኝ ደቂቃዎች ያህል ነበር።
የአሜሪካ ደህንነት አገልግሎት በወቅቱ የተኩስ ልውውጥ እንደነበረ አረጋግጧል፡፡
በትግስት ዘላለም
ነሀሴ 5 ቀን 2012 ዓ.ም
