ከሰሞኑ በክልሉ ላይ ሁሉት ሴቶች ማንነታቸው አልታወቁም በተባሉ ግለሰቦች ጥቃት ሳቢያ ህይወታቸው ሊያልፍ መቻሉን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል፡፡
የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ም/ሃላፊ ኦቶው ኦኮት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት ግለሰቦቹ ከሰሞኑን በሁለት ሴቶች ላይ በፈፀሙት ጥቃት ሳቢያ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል፡፡
ድርጊቱን ተከትሎ የክልሉ ፓሊስ ባደረገው ምርመራና ማጣራት ጥቃት አድርሰዋል የተባሉ ግለሰቦችን ተከታትሎ መያዝ መቻሉንና እነዚህ ግለሰቦችም ክስ እንዲመሰረትባቸው የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን ነግረውናል፡፡
ከድርጊቱ ጋር ተጠርጣሪ የሆኑ አካላት አብዛኛዎቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ነው የነገሩን፡፡
የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የአካባቢው ወጣቶች በመቆጣት በከተማዋ ሊፈጠር የነበረ ግርግር ቢኖርም የሃገር ሽማግሌዎችና የፀጥታ አካላት በጋር በመሆን ሁኔታውን ማረጋጋታቸውን ተናግረዋል።
አሁን ላይ ከተማዋ ወደ ቀደመ ሰላሟ መመለሷን ሰምተናል፡፡
በየውልሰው ገዝሙ
ነሀሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም
