የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዘዳንት ጀነራል አብዱል ፋታህ አልቡርሃን አስመራ ገቡ።

ገነራል አልቡርሃን ዛሬ ረፋድ አስመራሶደርሱ የኤርትራው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ሁለቱ መሪዎች በአስመራ በአስመራ-ሱዳን ሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ እንደሚመክሩ በአዲስ አበባ የሚገኘው የኤርትራ ኢምባሲ አስታውቋል።

ፕሬዘዳንት ኢሳያስ ከአንድ ወር በፊት ወደ ሱዳን ካርቱም አቅንተው በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረው መመለሳቸው አይዘነጋም።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ጷግሜ 2 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *