ተማሪዎቿን ወደ ትምህርት ገበታ የመለሰችው ደቡብ አፍሪካ 500 ተማሪዎችን ወደ ኳራንቲን አስገባች።

በደቡብ አፍሪካ አንድ ትምህርት ቤት የኮሮና ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ ወደ አምስት መቶ የሚጠጉ ተማሪዎች ኳረንቲን እንዲገቡ መደረጉ ተሰምቷል፡፡

በደቡብ አፍሪካ በርገርስድሮፕ በተባለች ከተማ ውስጥ በሚገኝ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ተከትሎ ነው አምስት መቶ የሚጠጉ ተማሪዎች ኳረንቲን እንዲገቡ የተደረጉት፡፡

የከተማዋ ባለስልጣናት እንደሚሉት ቫይረሱ ወደ ማህበረሰቡም በስፋት ሳይዛመት አልቀረም ተብሏል።

ባለስልጣናቱ አክለውም ወረርሽኙ በትምህርት ቤቱ በዚህን ያህል እንዲዛመት ምክንያት የሆነው ሁለት ተማሪዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ካረጋገጡ በኋላ ለትምህርት ቤቱ ባለማሳወቃቸው ነው፡፡

እንደውም በትምህርት ቤቱ ማስክ አይደረግም ፣አካላዊ እርቀትም አይጠበቅም ዋነኛው መንስኤ መሆን ያለበትም ይህ ነው በማለት ትምህርት ቤቱን ወቅሰዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ አስራት
መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *