ፕሬዘዳንት ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ባደረጉባቸው ግዛቶች ከ700 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መሞታቸው ተነገረ፡፡

በዶናልድ ትራምፕ ዘመቻ ምክንያት ከ700 በላይ ሰዎች ለሞት መዳረጋቸው ነው የተገለጸው፡፡

ይህም ለአሜሪካ ታላቅ ኪሳራ ስለመሆኑም የዘርፉ ሃኪሞች እየተናገሩ ነው የሚገኙት፡፡
ትራምፕ የምረጡኝ ዘመቻ ባደረጉባቸው አካባቢዎች የኮሮና በሽታ በከፍተኛ ደረጃ የመስፋፋት ምልክት መታየቱ ተመላክቷል።

በዘመቻው ወቅት ኮሮና ዋነኛ አጀንዳ ነበር። ባይደን በትራምፕ ድክመት ሳቢያ አሜሪካዊያን ከባድ ዋጋ እየከፈሉ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ ተናግረዋል።

የዘመቻው ተሳታፊዎች በበሽታው ተይዘው ቤት ላሉትም ይዘው መሄዳቸው አነጋጋሪ ሆኗል።

እስካሁን ባለው አሜሪካ 9 ሚሊዬን ዜጎቿ የኮቪድ 19 ተጠቂ ሆነዋል። 230ሺዎቹ ደግሞ ህይወታቸው ማለፉን የዓለም ጤና ደርጅት በድረገጹ አስታውቋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *