የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል እንደፈለጉ እየገቡና እየወጡ ነው ተባለ፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፓርቲ ኢዜማ በክልሉ የተፈጠረውን ጦርነት ተከትሎ ወደ ስፍራው ባቀናበት ወቅት የኤርትራ ወታደሮች ሲንቀሳቀሱ ተመልክቻለሁ ብሏል፡፡

ፓርቲው የአካባቢው ነዋሪዎች ነገሩኝ ብሎ እንደተናገረው ባሁኑ ሰአት የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል እንደፈለጉ ይንቀሳቀሳሉ ሲል አስታውቋል፡፡

እንደዚሁም የሁመራ አካባቢ ነዋሪዎች ለፓርቲው እንደተናገሩትም የኤርትራ ወታደሮች ባካባቢው ባይገኙ ኖሮ በነዋሪው ዘንድ ከፍተኛ እልቂት ይፈጠር ነበር ሲሉ ነግረውናል ሲል ነው ፓርቲው ያስታወቀው፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፓርቲ ኢዜማ ወደ ኮንሶ፣ መተከል፣ ማይካድራ እና መቐለ ልዑክ ቡድን በመላክ በስፍራዎቹ የተፈጠረውን ሁኔታ ለማጣራት ሙከራ አድርጎ በዛሬው እለት ምልከታውን ይፋ አድርጓል፡፡

ወደ መቐለ የተጓዘው የኢዜማ ከፍተኛ ቡድን በመጠለያ ያሉ ወገኖች ተዟዙሮ ከማየት ጎን ለጎን በቦታው ከነበሩ የፌደራል መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲሁም ከተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ጋር አሁን ስላለው ነባራዊ ሁኔታ እና መፍትሔዎች ላይ ውይይት ማድረጉን ገልጿል፡፡

ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከዶ/ር ሙሉ ነጋ ጋር በመገናኘት ‹‹በክልሉ አመራር የነበሩ ታዋቂ ፖለቲከኞችን ፤ ታዋቂ ግለሰቦችን እና የሌሎች ፓርቲዎች አባላት በመዋቅሩ ውስጥ አካተው ቢጠቀሙባቸው ጥሩ እንደሚሆን ፓርቲው ተቁሟል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 4 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *