በኢትዮጵያ ቆላማ አካባቢዎች የወፍ መንጋ ተከሰተ።

የግብርና ሚኒስቴር ለ ኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በቆላማ አካባቢዎች ላይ የወፍ መንጋ መራባቱን አስታውቋል፡፡

የሚኒስቴሩ የእጽዋት ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ በላይነህ ንጉሴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት በቆላማ አካባቢዎች ላይ የተራባ የወፍ መንጋ አለ፡፡

በስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች ላይ የተከሰተውን ይህንን የወፍ መንጋ ለመከላከል የሚያስችል ኬሚካል የአውሮፕላን ርጭት ለማካሄድ እንቅስቃሴ መጀመሩን ነግረውናል፡፡

የወፍ መንውጋን በትክክል መቆጣጠር ካልተቻለ መቶ በመቶ ሰብልን ማውደም የሚችል አቅም እንዳለው የነገሩን አቶ በላይነህ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ወፎች በሰብሎች ላይ በአንድ ጊዜ በማረፍ እስከ 20 ግራም ሰብልን የማውደም አቅም እንደላቸው ነግረውናል፡፡

የማደሪያ ቦታቸው ተለይቶ የኬሚካል ርጭቱን ለማካሄድ ማደሪያ ቦታቸውን የመፈለጉ ስራ እየተሰራ ይገኛልም ብለውናል፡፡

ከኮንሶ ተነስቶ ወደ ዝዋይ፤ሸዋሮቢት እና ኮምቦልቻን ያካለለ በየዓመቱ በሚሊኒየኖች የሚቆጠሩ የወፍ መንጋዎችን የመከላከሉ የኬሚካል ርጭት ስራ እንደሚሰራ እና ለዚህ አገልግሎት የሚውሉ አውሮፕላኖች እየተዘጋጁ መሆኑን ነግረውናል፡፡

የዝናብ ሁኔታ ምቹ በሚሆኑባቸው በቆላማ አካባቢዎች ላይ እነዚህ ወፎች የመራባት እድል እንዳላቸውና ይህም በጊዜ ካልተፈታ አስቸጋሪ ስለሚያደርገው የርጭት ስራውን ለማከናወን እንደሚሰራ ኢትዮ ኤፍ ኤም ከግብርና ሚኒስቴር ሰምቷል፡፡

በየውልሰው ገዝሙ
የካቲት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *