የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና እና የአዉሮፓ አገራት እስራኤል በጆርዳን ስምጥ ሸለቆ እያፈረሰች ያለዉን የዜጎችን መኖሪያ ቤት እንድታቆም አሳሰቡ።

የመንግስታቱ ድርጅትና የአዉሮፓ አገራት እስራኤል በሁምሳ አል ባቂያ የመኖሪያ መንደር እያፈረሰ በመሆኑ ዜጎች እየተፈናቀሉ እንደሚገኙም አስታዉቀዋል፡፡

እስራኤል በጆርዳን ስምጥ ሸለቆ አካባቢ እደረገች ያለዉ የሰፈራ ግንባታ እንዳሳሰባቸዉ አገራቱ ባወጡት መግለጫ ቴል አቪቭን አሳስበዋል፡፡

ፈረንሳይ፤ እንግሊዝ፤ ኢስቶኒ፤ኖርዌይ እና አይርላንድ እስራኤል በተደጋጋሚ በምታከሂደዉ የሰፈራ ግንባታ ምክንያት ዜጎች እንዲፈናቀሉ ከማድረጉም በተጨማሪ የሰብዓዊ እርዳታን እያስተጓጎለች ነዉ ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

እስራኤል በዌስት ባንክ እና በጆርዳን ስምጥ ሸለቆ በምትገነባቸዉ ግንባታዎች ምክንያት በርካታ ዜጎች እንደሚፈናቀሉም አልጄዚራ ዘግቧል፡፡

በረድኤት ገበየሁ
የካቲት 20 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *