ከ18 አመት በታች ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የኮሮና ቫይረስ ክትባት አይሰጥም ተባለ።

ከ18 አመት በታች ለሆኑ ህፃናትና ታዳጊዎች የኮሮና ቫይረስ ክትባት አሁን ባለው ሁኔታ እንደማይሰጥ የጤና ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ይህም የሆነው የአለም ጤና ድርጅት ያለውን ጠቀሜታ እና ተፅዕኖ በሚገባ ግልጽ ስላላደረገ ነዉ ተብሏል፡፡

ነፍሰ ጡሮችን በተመለከተ ደግሞ ሙሉ መረጃውን ለራሳቸው ግልፅ በማድረግ ክትባቱ እንደሚሰጣቸው ተነግሯል።

እስካሁን አንድ ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ክትባቱን ማግኘታቸውንም ሰምተናል።

ኢትዮጵያ 2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶዝ የአስትራዜኒካ ክትባት ብታስገባም ሃገሪቱ ካላት የህዝብ ቁጥር አንፃር 20 በመቶው የሚሆነዉ ብቻ ክትባት እንደሚያገኝ መነገሩ አይዘነጋም፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በረድኤት ገበየሁ
መጋቢት 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *