እንግሊዝ ከቤኒን የወሰደቻቸውን ቅርሶች ከአንድ ክፍለ ዘመን በኋላ ልትመልስ መሆኗን ገልጻለች፡፡

ቅርሶቹ በቅኝ ግዛት ዘመን እኤአ በ1897 እንግሊዝ የቤኒን ንብረቶችን በመዝረፍ የወሰደቻቸው እንደሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ከንብረቶቹም መካከል በወቅቱ የቤኒኑ ንጉስ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ከነሃስ የተሰሩ ዘውዶች፤ ጌጣጌጦችና ሌሎችም ቁሳቁሶች እንደነበሩ ተጠቅሷል፡፡

የቤኒን መንግስት ንብረቶቹን ለማስመለስ በርካታ ለአመታትን በድርድር እንደከረመ የሚታወስ ሲሆን ከስምምነት የተደረሰውም በ2019 እንደሆነ ነው የተነገረው፡፡

ስለሆነም እንግሊዝ ቅርሶቹን ከቤኒን ከወሰደች ከ124 አመታት በኋላ ለባለቤቶቹ ልትመልስ መሆኗን የዘገበው ሮይተርስ ነው፡፡

በጅብሪል ሙሃመድ
መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *