ቻይና በምእራቡ አለም ለተጣለባት ማእቀብ የአጸፋ እርምጃ መዉሰድ ጀመረች፡፡

ቻይና በአሜሪካና በአውሮፓ ህብረት የተጣለባትን ማእቀብ አንደ አስተማሪ ቅጣት ሳይሆን በጋራ የተደረገብኝ አድማ ነው ስትል ወቅሳለች፡፡

አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት ቻይና ዢንጃንግ በተሰኘው የሀገሪቷ ክፍለ ሀገር በሚኖሩ አናሳ የሙስሊምና ሌሎችም ህዝቦች ላይ ያልተገባ ሰብአዊ መብቶች አያያዝ አሳይታለች በሚል ያሳለፍነው ሳመንት ማእቀብ መጣላቸዉ ይታወሳል፡፡

የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራትና አሜሪካ ማእቀቡን ለማስቀመጣቸው ምክንያት ናቸው የተባሉትን ቻይና ማስተባበሏም የሚታወስ ነው፡፡

የዢንጃን ክፍለ ሀገር ሃላፊው ዡ ጉይዣንግ በተለይ በአውሮፓ ህብረትና በአሜሪካ በኩል የቻይና ባለስልጣናት የዘር ማጥፋ ወንል ሙከራ አድርገዋል የተባለው ስህተት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ስለሆነም የቻይናን ሉአላዊነትና ስም የማጥፋት ዘመቻ ተደርጎብናል ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

ቢሆንም ግን ቻይና ማእቀብ አድራጊዎችን በቃላት ጦረርነት ብቻ ከመግጠምም ባለፈ የአውሮፓ ህብረት ሊቀመንበር ሬንሀርድ ቢቲኮፈርን ጨምሮ በ10 ባላስልጣናት ላይ ማእቀብን በመጣል የበቀል እርምጃ መዉሰድ ጀምራለች ተብሏል፡፡

በዚህም ቻይና ከምዕራቡ ዓለም ጋር ለምታደርገው ዲፕሎማሲዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ትልቅ ክፍተትን የፈጠረ አጋጣሚ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ቻይና በአለም የኢኮኖሚ መሪ ለመሆን በምትሯሯጥበት በአሁኑ ሰአት በአሜሪካ፤ በካናዳ ብሎም በአውሮፓ ህብረት የጋራ ኢኮኖሚያዊ ማእቀብ የሚጣልባት ከሆነ ደግሞ ሩጫዋን ሊገታው እንደሚችል አስተያየት እየተሰነዘረበት ይገኛል፡፡

ምንጭ፡-ሮይተርስ

በጅብሪል ሙሃመድ
መጋቢት 20 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *