በሚያዚያ ወር የነበረው የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ የግንቦት ወር የመሸጫ ዋጋ ሆኖ እንዲቀጥል ተወሰነ፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስቴር በድረ-ገጹ እንዳስነበበዉ፣ ከአውሮፕላን የነዳጅ ምርቶች ውጭ ያሉ ሌሎች የነዳጅ ምርቶች በሚያዚያ ወር ሲሸጡበት በነበረው ዋጋ የግንቦት ወር የመሸጫ ዋጋ ሆኖ እንዲቀጥል መወሰኑን ገልጿል፡፡

የአውሮፕላን የነዳጅ ምርቶች ዋጋ የአለም የነዳጅ ዋጋን መሰረት በማድረግ ተሰልቶ የተገኘው 11 ሣንቲም በመጨመር በሚያዚያ ወር ሲሸጥበት ከነበረው 43.70 ወደ ብር 43.81 ከፍ እንዲል መወሰኑንም አስታዉቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሚያዝያ 28 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *