በቤንች ሸኮ ዞን በተለይም በጉራፈርዳ ወረዳ በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ታጣቂዎቹ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን እየፈጸሙ በመሆኑ ቁጥራቸው ያልተገለጸ ሰዎች አካባቢያቸውን ጥለው በመሸሽ ላይ እንደሆኑ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
በዞኑ የመሸገው የሽፍታ ቡድን ቡድን ዜጎች በብዛት በሚኖሩባቸው አካባቢዎች እየተንቀሳቀሱ የዜጎችን ህይወት እየቀጠፉ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
ታጣቂዎቹ ለህብረተሰቡ ብቻ ሳይሆን ለጸጥታ አካሉም ጭምር የስጋት ምንጭ እንደሆኑ ቀጥለዋል ሲሉም ተናግረዋል አቶ ፍቅሬ አማን፡፡
እነዚህ ታጣቂ ቡድኖች ከአካባቢው ለማጥፋት የጸጥታ አካላት የተጠናከረ ስራ እየሰሩ ቢሆንም በአካባቢው ያለው የጸጥታ አካል በቂ ባለመሆኑ ታጣቂዎቹ ለህብረተሰቡ ብቻ ሳይሆን ለጸጥታ አካሉም ጭምር የስጋት ምንጭ እንደሆኑ አቶ ፍቅሬ ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ በዞኑ ያለው የጸጥታ ሁኔታ የሚያሰጋ ባይሆንም ህብረተሰቡ ግን ስጋት ላይ እንደወደቀ የዞኑ አስተዳዳሪ ነግረውናል፡፡
ሄኖክ ወ/ገብርኤል
ግንቦት 17 ቀን 2013 ዓ.ም
