እነ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች የባልዳራስ አመራሮች በምርጫ ሊሳተፉ ነው።

የባልደራስ አመራሮች በዘንድሮው ምርጫ እንዲሳተፉ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ እያስፈፀምኩ ነው ሲል ምርጫ ቦርድ ፍርድ ቤት ቀርቦ አስረድቷል ።

ዛሬ ችሎት ቀርበው ጉዳዪን ያስረዱት የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ ብርቱካን ሚደቅሳ ቦርዱ ውሳኔውን እየፈጸሙ መሆኑን አስረድተዋል ።

በዚህም ምርጫ ቦርድ 3.5 ሚሊዮን ተጨማሪ ወጪ አውጥቼ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ እየፈጸምኩ ነው ብሏል።

የባልዳራስ አመራሮችም ፓርቲው ወክለው እንዲወዳደሩ ቀሪ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነም ፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ለኢትዮኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ግንቦት 26 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *