ግብፅ ፣ ናይጄሪያ ፣ ደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በመሳብ ቀዳሚ አገራት ሆነዋል፡፡

ግብፅ ፣ ናይጄሪያ ፣ ደቡብ አፍሪካ ፣ ሞዛምቢክ ባለፉት አስር ዓመታት ከፍተኛ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንቶችን የሳቡ ቀዳሚ የአፍሪካ አገራት ዝርዝርን ይመራሉ አንድ አለም አቀፍ የኢኮኖሚ ተቋም አስታወቀ ፡፡

ከዓለም ባንክ በተገኘው መረጃ መሠረት አስሩ አገራት እ.ኤ.አ. ከ 2011 እስከ 2020 ባሉት ዓመታት ውስጥ ከ 300 ቢሊዮን ዶላር በላይ የተጣራ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ መቻላቸው ተገልጿል ፡፡

እንደ ኢኮኖሚያዊ ትብብር እና ልማት ድርጅት (OECD) መረጃ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለመሳብ በራቸውን ክፍት በማድረግ ውጤታማ የሆነ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ስርዓት ወሳኝ እና ለሀገር እድገት ተመራጭ እንደሆነ ጠቅሷል ፡፡

በተደረገው ጥናት መሰረት ግብጽ በድምሩ 56.2 ቢሊዮን ዶላር በመሳብ ሁለተኛ አገር ስትሆን ፣ በአፍሪካ የግዙፍ የኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችውን ናይጄሪያን ደግሞ በ 45.1 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በመሳብ ቀዳሚ አገር ሆናለች፡፡

ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ቀጥታ የውጭ መዋዕለ ንዋይ ፍሰት ዋና ተፎካካሪ የሆነችው ደቡብ አፍሪካ በአስር ዓመታት ጊዜ ውስጥ የ 41.3 ቢሊዮን ዶላር የሳበች ሲሆን ሞዛምቢክ በ 37.17 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት በመሳብ ትከተላለች ፡፡

ጋና (32.5 ቢሊዮን ዶላር) ፣ ሞሮኮ (27.1 ቢሊዮን ዶላር) ፣ ኮንጎ ሪፐብሊክ (21.4 ቢሊዮን ዶላር) ፣ ኢትዮጵያ (20.8 ቢሊዮን ዶላር) ፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ (13.59 ቢሊዮን ዶላር) ፣ እና አልጄሪያ (12.4 ቢሊዮን ዶላር) በመሰራት ይገኙበታል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
ግንቦት 27 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *