በአዲስ አበባ ነገ ሐሙስ እና በቀጣይ ቀናቶች በአንዳንድ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ይቋረጣል ተብሏል፡፡

በዚሁ መሰረት፡-

ሐሙስ ሰኔ 24 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ድረስ፤

• ከጎላጎል ወደ መገናኛ፣ በገቢዎች፣ በቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል፣ በሻላ መናፈሻ፣ በቦሌ ጤና ጣቢያ፣ በመገናኛ በከፊል እና አካባቢዎቻቸው፤
በዚሁ ቀን ከቀኑ 6፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ፣

• በአፍንጮ በር፣ በአራተኛ ፖሊስ ጣቢያ፣ በጊዮርጊስ ቤተ-ክርስትያን፣ በአትክልት ተራ፣ በአንዋር መስጊድ፣ በራጉኤል ቤተ-ክርስትያን፣ በደጃች ውቤ ሰፈር፣ በመርካቶ እና አካባቢዎቻቸው፤

በተመሳሳይ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ፣

• በገነት ሆቴል፣ በኦርቢስ፣ በኦኤዩ፣ በጮራና ጋዝ፣ በሜክሲኮ አካባቢ፣ በለገሃር፣ በጊዮን፣ብሄራዊ ሆቴል፣ በእስጢፋኖስ፣ በሳልኮስት፣ በፍትህ ሚኒስቴር፣ በስታድየም፣ በካዛንቺስ በከፊል፣ በሴቶች አደባባይ፣ በአቧሬ፣ በመለስ ፋውንዴሽን፣ በእንደራሴ ኮንደሚኒየም፣ በጎተራ፣ በላንቻ፣ በግሎባል ሆቴል፣ በጨርቆስ ቤተ-ክርስትያን እና አካባቢዎቻቸው፤

ዓርብ ሰኔ 25 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ፤

• በሰሚት፣ በፍሊንት ሰቶን፣ በወርጂ ሰፈር፣ በሰሚት ለስላሳ እና አካባቢዎቻቸው፤
እንዲሁም ቅዳሜ ሰኔ 26 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ድረስ፤

• በሰንጋ ተራ፣ በቴዎድሮስ አደባባይ፣ በንግድ ማተምያ ቤት፣ በፒያሳ፣ በኤክስትሪም ሆቴል፣ በተክለ-ሀይማኖት ሆስፒታል፣ በሀግቤስ፣ በአዲሱ ሚካኤል፣ በፓውሎስ ሆስፒታል፣ በሞተራ ሆቴል፣ በጨው በረንዳ፣ ከመርካቶ እስከ ሰባተኛ እና አካባቢዎቻቸው፤

በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ፣

• በዲ አፍሪክ ሆቴል፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ በተክለ-ሀይማኖት ቤተ-ክርስትያን፣ በጎማ ቁጠባ፣ በለገሃር፣ በቴሌ ባር፣ በራስ ሆቴል፣ በአምባሳደር፣ በሸራተን፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በኮሜርስ፣ በፋና፣ በፖስታ ቤት፣ በጥቁር አንበሳ እና አካባቢዎቻቸው፤

በተጨማሪም እሁድ ሰኔ 27 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ድረስ፤

• በወይብላ ማርያም፣ በአንፎ፣ በአውግስታ፣ በወይራ ሰፈር፣ በወይራ ኮንደሚኒየም፣በሞቢል፣ በራሽያ ካምፕ፣ በተዘንኣ ሆስፒታል፣ በሙስና ሰፈር፣ በአየር ጤና፣ በሳሚ ካፌ ጀርባ፣ በታቦት ማደሪያ፣ በመሃንዲስ ሰፈር እና አካባቢዎቻቸው፤

በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ፤

• በገነት ሆቴል፣ በኦርቢስ፣ በኦኤዩ፣ በጮራና ጋዝ፣ በሜክሲኮ፣ በአፍሪካ ህብረት፣በመቻሬ፣ በካርል አደባባይ፣ በሜክሲኮ፣ በታንባሆ ሞኖፖል፣ በሳር ቤት፣ በቴሌ፣በመብራት ኃይል ክበብ ጀርባ፣ በዲ አፍሪክ ሆቴል፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣በተክለ-ሀይማኖት ቤተ-ክርስትያን፣ በጎማ ቁጠባ እና አካባቢዎቻቸው

በመሆኑም በእነዚህ ቀናቶች በመካከለኛ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የኤሌክትሪክ የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ፣ ክቡራን ደንበኞቻችን ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ሰኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *