በቀጣይ መንግስት የሚሆነው ፓርቲም ሌብነትን ማጥፋት ቀዳሚው ትኩረት ሊሆን እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
ከህዝብ የሚዘርፉ አካላት የሥራ ዕድሎችንና ሌሎች ዘርፎችን ሲደግፉ ሳይሆን የምንመለከተው የዘረፉትን ገንዘብ በመጠጥ ቤቶችና በሺሻ ነው የሚበትኑት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ፣በሌብንት ህዝቡን እያማረርን ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
በመሆኑም ሌብነትን የሚታገልና የሚያጠፋ ትውልድ መፍጠር ያስፈልጋል ሌብነት የብልጽግናም የሀገርም ጠንቅ ነው፡፡
በተለይ አዲስ አበባን እየበዘበዛት ያለው ሌብነት ነው፡፡ስልጣንን በገንዘባቸው መግዛት የሚፈልጉ ግለሰቦችም እንዳሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ አንስተዋል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
አባቱ መረቀ
ሰኔ 28 ቀን 2013 ዓ.ም
