ከኦሮሚያ ጋር በምንዋሰንባቸው አካባቢዎች የሚንቀሳቀሰውን አሸባሪው ሸኔ በተለይ በአማሮ ልዩ ወረዳ በተደራጀ ሁኔታ አልፎ አልፎ ጥቃት እያደረሰ እንደሆነ የደቡብ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው የስልክ በነበራቸው ቆይታ ነግረውናል፡፡
በአማሮ ልዩ ወረዳ ፤በጉጂ ልዩ ወረዳ ፤በኮንሶ ኩታ ገጠም አካባቢዎች እና በማዕከላዊ ዞኖች እንደ ሶዱ አጎሽቴ አካባቢ የአሸባሪው ሸኔ ‘ሴል’ እንዳለ ምልክት አለ ያሉት ሃላፊው ፣በጥቃቱ ለእርሻ በወጡ ሰዎች ጭምር ተገድለዋል፣ ንብረት መውደሙን ነግረውናል፡፡
አጥፊውን ሀይል በተደራጀ እና በተቀናጀ ሁኔታ ለማስወገድ የሁለቱ ክልል መንግስታትም የፀጥታ ሀይሉን በማቀናጀት የህግ ማስከበር ዘመቻ እያደረግን በመሆኑ በዚህም እንደ ከዚህ ቀደሙ የከፋ ጥቃት እየደረሰ አለመሆኑን አንስተው፣ አሁንም ቢሆን ከፍተኛ ትኩረት የሚሹ ነገሮች አሉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
ያይኔአበባ ሻምበል
ሐምሌ 28 ቀን 2013 ዓ.ም
