የታሊባን ታጣቂዎች በስድስት ቀናቶች ውስጥ ስምንት ግዛቶችን ተቆጣጠሩ

የአፍጋኒስታን መንግስት ባለፉት ስድስት ቀናቶች በርካታ ግዛቶቹ በታሊባን ታጣቂዎች የተነጠቀ ሲሆን በትላንትናው እለት ደግሞ ፋይዛ አባድን የተባለችውን ግዛት ተቆጣጥረዋል፡፡

የአሜሪካ ወታደሮች ሀገሪቷን ጥለው መውጣታቸው ተከትሎ ታሊባን ግዛቱን እያስፋፋ በመሆኑ የአሽራፍ ጋኒ መንግስትን ስጋት ከመሆን በዘለለ ለአፍጋኒስታን አጋር ለሆኑ ሀገራት ጭምር ስጋት መሆኑን ነው ተነግሯል፡፡

አፍጋኒስታንን እያስጨነቀ የሚገኝው ታሊባን በአሁኑ ሰአት በሀገሪቱ እጅግ ከባድ የተባለ የእስልምና ህግ መጣሉን ነው አልጀዚራ ያስነበበው፡፡

አሜሪካ ከሀገሪቷ ከወጣች በኋላ የታሊባን 65 በመቶ የሚሆነውን የአፍጋኒስታን ግዛት በስሩ አድርጓል፡፡

በአፍጋኒስታን የሚገኝው የአውሮፓ ህብረት ተወካይ እንዳስታወቀው ታጣቂ ቡድኑ ወደ ካቡል በከፍተኛ ሁኔታ እየገሰገሰ ይገኛል ሲል አስታውቋል፡፡

የታሊባን ግስጋሴን ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አፍጋኒስታናዊያን ሀገራቸውን ከታጣቂ ቡድኑ ነጻ ማውጣት አለባቸው ብለዋል፡፡

አሜሪካ ባለፉት 20 አመታት አንድ ትሪሊየን ዶላር ፈሰስ ያደረገች ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን ሕይወት መገበሯን ገልጸው ፤አሜሪካ ወታደሮቿን ለማስወጣት ያሳለፈችውን ውሳኔ አትቀለብሰውም ብለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

ሔኖክ ወ\ገብርኤል
ነሐሴ 05 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *