የከተማ አስተዳደሩ ከቀን 07/12/2013 ዓ.ም ጀምሮ መሬት ነክ አገልግሎትን አግዶ መቆየቱ ይታወቃል።
ጊዜያዊ እግዱ አሁን የተነሳ በመሆኑ አገልግሎቱን ከቀን 13/05/2014 ዓ.ም ጀምሮ በየክ/ከተማው ማግኘት ይቻላል።
ታግደው ከነበሩ አገልግሎቶች መካከል ጊዜያዊ እግድ የተነሳላቸው አገልግሎቶች ዝርዝር ከዚህ በታች የተገለጹት ናቸው ፦
- ህጋዊ ሰነድ ላላቸው ይዞታዎች ብቻ ዋስትና እዳ መመዝገብ
- የፍርድ ቤት እና የባንክ እግድ የመመዝገብና የመሰረዝ አገልግሎት
• የእዳና እገዳ የማጣራት አገልግሎት - የስመ ንብረት ዝውውር ስራ
• በባንክ ሐራጅ የተሸጠ
• በፍ/ቤት አፈፃፀም የተሸጠ
• የኮንዶሚኒየም ቤት የስም ዝውውር አገልግሎት
• በውርስ የተላለፈ ንብረት
• በReal estates አልሚ የተፈፀመ የቤት ሽያጭ - ለነባር ይዞታዎች የቦታ ኪራይና የቤት ግብር ተመን
- የንብረት ግመታ
- በይዞታ ይገባኛል ክርክር በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማስረጃ መስጠት
- የወሰን ይመላከትልኝ /የወሰን ችካል/
- በከተማ አስተዳደር የሚታወቅ እና ቅድሚያ የሚሰጥ የልማት ተነሺ አገልግሎት
• ካሣ ክፍያ
• ምትክ ቤት
• ምትክ ቦታ አሰጣጥ አገልግሎቶች - የቦታ ዝግጅት
- የወሰን ማስከበር ተግባራት
- በሊዝ በተላለፈ ቦታ ላይ የግንባታ ክትትል
- የለማ መሬት በምደባ ወይም በጨረታ ማስተላለፍ
- አዲስ ካርታ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች
• የምትክ ኮንዶሚኒየም ቤት ለተወሰነላቸው
• ለአመራር የሚሰጡ ኮንዶሚኒየም ቤቶች፣
• የReal estates ተጠቃሚዎች /ቤት ገዥዎች የተናጠል ካርታ
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ጥር 17 ቀን 2014 ዓ.ም
