አቢሲኒያ ባንክ እና ቪዛ ያዘጋጁት ‹‹የአቢሲኒያ ቪዛ ካርድን ይጠቀሙ፤የቶታል ኢነርጂ የአፍሪካ ዋንጫ 2021 የጉዞ ዕድልን ያሸንፉ” ባለእድለኞች የሽኝት ስነስርአት ተካሂዶላቸዋል፡፡
የቪዛ ካርድ ጠቀሜታዎችን ለገበያ ለማስተዋወቅ ከቪዛ ጋር ጥምረት መመስረቱን ያስታወቀው አቢሲኒያ ባንክ እድለኞቹ ካሜሮን ላይ እየተካሄደ የሚገኘውን የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታን ለመከታተል እንደሚችሉም አስታውቋል፡፡
ጥር 18 ቀን 2014 ዓ/ም በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ የዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት መካሄዱን ያስታወሰው ባንኩ የምሥራቅ አ.አ. ዲስትሪክት ሁለት ደንበኞቹ የዕጣው ባለ ዕድል መሆናቸውንም አስታውቋል፡፡
ባለ ዕድለኞች ወደ ካሜሮን ጉዞ እንዲያደርጉ የሚያስችላቸው የጉዞ ዝግጅት በማጠናቀቃቸውም የሽልማት እና የሽኝት ሥነ-ሥርዓት ማከናወኑንም ባንኩ አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም 42 ኢንች ቴሌቪዥኖችን፤ ስማርት የሞባይል ቀፎዎችን፤ ዲኮደሮችንና ሌሎች ስጦታዎች በሽልማቱ መካተታቸውን ባንኩ ለኢትዮ ኤፍኤም ያደረሰው ዘገባ ያመላክታል፡፡
አብዱልሰላም አንሳር
ጥር 27 ቀን 2014 ዓ.ም
