“አክሱምን እና ላሊበላን የገነቡ አባቶች ያሉን ኢትዮጵያውያን፣ ታሪክ ቀምረን ከታሪክ መማር አቅቶን በተሳሳቱና በተዛነፉ ታሪኮች እርስ በርስ መግባባት አለመቻላችን አሳፋሪ ነው “ ታዬ ደንደኣ

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንዳኣ አክሱምን እና ላሊበላን የገነቡ አባቶች ያሉን ኢትዮጵያውያን አኩሪ ታሪክ ቢኖረንም ይህን ታሪክ ቀምረን፣ ከታሪክ መማር ሲገባን በተሳሳቱና በተዛነፉ ታሪኮች እርስ በርስ መግባባት እንኳን ቸግሮናል ብለዋል። ሚንስትሩ ይህንን ያሉት “የታሪካዊነት አበርክቶ ለብሔራዊ መግባባት እና የታሪክ ምሁራን ሚና” የሚል ርዕስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በሰላም ሚኒስቴር በጋራ በተሰናዳ ውይይት ላይ ነው። […]

በአርጀንቲና ከ4 ቀን በፊት የተነሳው የሰደድ እሳት በ90 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚገኝን ብዝሀ-ሕይወት ማውደሙ ተገለጸ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

በአርጀንተና ደቡባዊ ክፍል ቹበት(Chubut) በተባለችው ግዛት አቅረቢያ በሚገኝ ጫካ ላይ የተነሳው የሰደድ እሳት በ90 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚገኝን ብዝሀ- ሕይወት ማውደሙ የሀገሪቱ ባለስልጣናት መናገራቸው ተዘግቧል፡፡ እሳቱ ያለማቋረጥ ለ 4 ቀንና ሌሊት እየነደደ በመቆየቱ ከ80 እስ 90 ሺህ ሄክታር መሬት የሚገኙ ዛፎችን ጨምሮ በውስጡ የሚገኙ ብዝሀ-ሕይወት ላይ ውደመት ማድረሱን ባለስልጣናቱ ገልጸዋል፡፡ የዚህ አይነት አውዳሚ የሰደድ […]

የዲጂታል መታወቂያ ህትመትና ስርጭት በክፍለ ከተማ ደረጃ ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ስራ እየሰራ መሆኑ ተነገረ

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ እንደገለጸው፣ የአዲስ አበባ ከተማ የዲጂታል የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት በማዕከል ደረጃ በማህተም ለሁሉም ክፍል ከተማ ሲያሰራጭ የነበረውን አሰራር ቀይሮ ህትመቱ በከተማ ባሉ በሁሉም ክፍለከተሞች ደረጃ ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎቱ አንድ ነዋሪ አንድ የነዋሪነት መታወቂያ ብቻ እንዲኖረዉ ማድረግ እንደሚያስችል አስታውቋል:: ይህ ስርዓት ለነዋሪዎች የማህበራዊ እና […]

“በሂሩት አባቷ ማን ነው ? “ ፊልም ላይ ለተሳተፉ ተዋንያን ጥሪ ቀረበ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በቀዳማዊ አጼ ሃይለስላሴ ተመርቆ ለመጀመርያ ጊዜ ለህዝብ የተበረከተው ሂሩት አባቷ ማን ነው? ፊልም ላይ የተሳተፉ ተዋንያን አሁን ላይ የት እንዳሉ አይታወቅም ተብሏል፡፡ የሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት እነዚህ ዜጎች የት እንደሚኖሩ በተለያዩ ጊዜያት ሲፈልግ እንደነበረ አስታውቋል፡፡አሁንም በፊልሙ የተሳተፉ አካላት ወይም ቤተሰቦቻቸው እስከ ጥር 5ቀን 2014 አመት ድረስ ጥቆማ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በኢትዮጵያ ታሪክ […]

የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ ተጣለ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ ጥሏል፡፡ ቢሮው በመዲናዋ በሞተር ብስክሌት ምክንያት የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎችንና ህገ ወጥ ድርጊቶችን መከላከል የሚያስችል የሞተር ብስክሌት ፈቃድና ቁጥጥር መመሪያ በማውጣት ወደስራ መገባቱ አስታውሷል። በአሁኑ ወቅት ውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ የቀረበውን ጥሪ […]

በመዲናዋ በደረሱ ሁለት ድንገተኛ አደጋዎች በሶስት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደረሰ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ በሁለት ክፍለ ከተሞች በደረሱ ድንገተኛ አደጋዎች በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የኮሚሽኑ የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ አቶ ጉልላት ጌታነህ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በከተማዋ በሁለት ቀናት ወስጥ በደረሱ አደጋዎች ምክንያት ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ የሚጠጋ ንብርት ለጉዳት ተዳርጓል ብለዋል፡፡ የመጀመርያው የእሳት አደጋ የደረሰው በኮልፌ ቀራኒዮ […]

በኬንያ የአልሸባብ ሃይሎች በከፈቱት ጥቃት 6 ሰዎች ሞቱ

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

በኬንያ የአልሸባብ ሃይሎች በከፈቱት ጥቃት 6 ሰዎች ሞቱ በኬንያ የወደብ ከተማ በሆነችው ላሙ (Lamu County) አካባቢ የአልሸባብ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት 6 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸው ከከተማዋ ኮሚሽነር ሰምቻለሁ ሲል ሲጂቴን ከደቂቃዎች በፊት ዘግቧል፡፡ ዘገባው አክሎ እንደገለጸው ከሆነ ታጣቂዎቹ በርካታ ቤቶችን ማቃጠላቸውንም አትቷል፡፡ የአሸባሪው የአልሸባብ ሃይሎች ሰዎችን የገደሉትም ጥይት በመተኮስ፤ በድብደባ እና ሰዎች ቤታቸው ውስጥ እንዳሉ በማቃጠል […]

ዐቃቤ ህግ በእነ እስክንድር ነጋ የክስ መዝገብ ላይ ባሰማኋቸው ምስክሮች ብይን ይሰጥልኝ አለ

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ዐቃቤ ህግ አሉኝ ብሎ በክሱ ላይ ከጠቀሳቸው ምስክሮች ውስጥ 6 ምስክሮን ያሰማ ሲሆን 7ኛ ምስክር የበተደጋጋሚ በተሰጠው ተለዋጭ ቀጠሮ አለመቅረቡን ተከትሎ በፖሊስ ታስሮ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ቢሰጥም ትዕዛዙ ሳይፈጸም፤ ምስክሩም ሳይቀርብ ቀርቷል፡፡ ችሎቱም በተደጋጋሚ ቀጠሮ ላልቀረበው ምስክር በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሊሰጥ አይገባም ሲል ብይን ሰጥቷል። በዚሁም መሰረት ዐቃቤ ሕግ እስካሁን ባሰማኋው ምስክሮች እና ባቀርብኳቸው ማስረጃዎች መሰረት […]

የሱዳን ወታደራዊ ሃይል በካርቱም የሚገኙ የአልአረቢያ እና የአልሃደስ ቴሌቪዥን ጣቢያዎችን መክበቡን እና ንብረታቸውንም መውረሱ ተዘግቧል፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

ወታደራዊው ሃይል ይህንን ሲያደርግም የሚያሳይ የሲሲቲቪ ተንቀሳቃሽ ምስልም በጣቢያዎቹ የሚገኙ ሰራተኞችን ሲያንገላቱ እና ጥቃት ሲሰነዝሩባቸው ያሳያል፡፡ በዱባይ መቀመጫውን ያደረገው አልአረቢያ ቴሌቪዥን በርካታ ጋዜጠኞቹ እና ሰራተኞቹ መጎዳታቸውን አስታውቋል፡፡ በካርቱም የህዝቡ አመፅ እና ተቃውሞው እንደቀጠለ ሲሆን ወታደራዊ ሃይሉ ተጨማሪ አራት ሰዎችን ሳይገድል እንዳልቀረም ተዘግቧ፡፡ በተለይም በኡምዱርማ እና በካርቱም ሰሜናዊ አካባቢዎች ተቃውሞውም የወታደሩም እርምጃ የከረረ እንደነበር በዘገባው ታትቷል፡፡ […]

የገንዘብ ሚኒስቴር በሁለት ወራት ውስጥ 70.6 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን አሳወቀ

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የገንዘብ ሚኒስቴር በጥቅምት እና ህዳር ወራት ከሃገር ውስጥ ገቢ 70.6 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን እና የእቅዱን 89.3 ከመቶ ማሳካቱን አስታወቀ፡፡ ባለፉት ሶስት ወራት በመንግስት ገቢና ወጪ ረገድ ጤናማ የፊሲካል አስተዳደር ተግባራዊ መደረጉን ያስታወቀው ሚኒስቴሩ የ100 ቀናት እቅድ አፈፃፀሙ መገምገሙን አስታውቋል፡፡ በፌዴራል መንግስት፣ ከሀገር ውስጥና ከልማት አጋሮች ለመሰብሰብ የታቀደውን የመንግስት ገቢ ለማሳካት ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ያስታወሰው ሚኒቴሩ […]