ቻይና ሆንኮንግ የራሷ ጦር እንዳይኖራት እና መገንጠልን የሚከለክል አዲስ የደህንነት ህግ ለማውጣት እየተዘጋጀች መሆኗ ተነግሯል ።

ሆንግ ኮንግን የተመለከተ አዲስ የሚወጣው የደህንነት ህግ ፣ ህዝብን በመንግስት ላይ ማነሳሳት ፣ የመገንጠል ጥያቄ እና ሃገርን መክዳትን በጥብቅ የሚከለክል ነው፡፡

ለ150 አመታት በእንግሊዝ ቀኝ ግዛት ስር የነበረችው ሆን ኮንግ ፣ አሁን በስራ ላይ ያለው ህግ የውጭ ግንኙነት እንዳታድርግ እና የእራሷ መከላከያ ሰራዊት እንዳይኖራት ከመከልከል ውጭ ሌሎች መብቶች ላይ ገደብ እንደማይጥል ተነግሯል ።

የሆንኮንግ ጉዳይ የሚከተሉት እና የ ቻይናን መንግስት በመቃወም የታውቁ ግለሰቦች ሆንኮንግ እርሷን ማስተዳደሪያ ህግ እና ድንበር ያላት ግዛት ናት ቻይና ይህን መብቷን የሚጋፍ አዲስ ህግ ለማውጣት ማቀዷ ታሪካዊ ስህተት ነው ብለዋል ።

ቢቢሲ እንደዘገበው ፤ የቻይና መንግስት በኩሉ አዲስ ህግ ማውጣት ያስፈለገበት ዋና ምክንያት ሆንኮግን ሽብርተኞት ለመከልከል እና የውጭ ጣልቃ ገብነትን ለመገደብ እንድሆነ ተናግሯል ።

በቻይና በፈረንጆቹ 2019 ተጀምሮ ለ 7 ወራት የዘለቀው መንግስታዊ ተቃሞ ፣ በ ኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ተቀዛቅዟል ፣ ሀገሪቱም ተቃውሞውን አስተባብረዋል መርተዋል ያለችውን ሰዎች እያሰረች መሆኑ ተነግሯል ።

በቅርቡ ይውጣል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ አዲስ ህግ ቻይናን ወደ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እንዳይከታት ተስግቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሆንግ ኮንግ አክቲቪስቶች አዲሱን የቻይና ደህንነት ህግ በመቃወም ህዝቡን ለተቃውሞ ጠርተዋል፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው ቻይና የሆንግ ኮንግን ብሄራዊ የደህንነት ህግ በሚጻረር መልኩ አዲስ የደህንነት ህግ ለማዘጋጀት በማቀዷ ነው አክቲቪስቶቹ በኦንላይን ተቃውሞ የጠሩት፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በዳንኤል መላኩ
ግንቦት 14 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *