የዋሸንግተን ፖሰት አምደኛው ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ባሳለፍነው ዓመት ነበር በቱርክ ኢስታንቡል በሚገኘው የሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ ውስጥ በሳውዲው ንጉስ ቅጥረኛ ገዳዮች የተገደለው።
ለጋዜጠኛው ሞት ምክንያት ደግሞ የሳውዲ አረቢያ ንጉሳዊያን ቤተሰቦችን ቅሌት ለዓለም አጋልጠሃል በሚል ሲሆን ይህ ግድያ ቱርክን ክፉኛ አስቆጥቶ ለሁለቱ አገራት ወዳጅነት መቀዛቀዝ ትልቅ ምክንያትም ሆኗል።
የዚህ ሟች ጋዜጠኛ ልጆች ለአባታቸው ገዳዮች ይቅርታ ማድረጋቸውን አሳውቀዋል።
የካሾጊ ልጅ የሆነው ሳላህ እና ቤተሰቡ እንዳሉት የአባቴን ገዳዮች ይቅር በማለት ከፈጣሪያችን ሽልማት እንፈልጋለን ሲሉ ተናግረዋል።
የካሾጊ ልጅ ሳላህ ይህን የይቅርታ ንግግር በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል ሲል አልጄዚራ ዘግቧል፡፡
“በዚህ በተባረከች ወር (ረመዳን) የፈጣሪን ቃል ማስታወስና ማሰብ የግድ ነው ያለው ሳላህ አንድ ሰው ተበዳይም ቢሆን በዳይ ይቅር ቢያደርግ ሽልማቱ ከአላህ ዘንድ ነው ብሏል።
በተጨማሪም ወንዶች ልጆች ሟች አባታችን ጀማል ካሾጊን የገደሉትን ሰዎች ይቅር በማለት ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ ሽልማት እንሻለን ብለዋል ፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በደረሰ አማረ
ግንቦት 14 ቀን 2012 ዓ.ም











