ግብጽ በሁሉም ሆስፒታሎቿ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ልትጀምር መሆኑን አስታወቀች፡፡

በሃገሪቷ ያሉ 320 አጠቃላይ ሆስፒታሎች የበሽታው ምልክት ለታየባቸው ሰዎች ምርመራ ያደርጋሉ ነው የተባለው፡፡

መንግስት ትናንት እንዳስታወቀው ቀለል ያሉ የበሽታው ምልክቶች የታዩባቸው ሰዎች ቤታቸው ሆነው የምርመራ ውጤታቸው ይጠብቃሉ፡፡ከባድ ምልክቶችን ያሳዩ ሰዎች ግን ሆስፒታል ይቆያሉ ብሏል፡፡

እንደ ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘገባ ከፈረንጆቹ ግንቦት 14 ጀምሮ ቀላል ምልክቶች የታዩባቸው ጥቂት ሰዎች በሆስፒታል ከመቆየት ይልቅ ቤታቸው ሆነው ራሳቸውን አግልለው እንዲቆዩ ጠይቀዋል፡፡

ግብጽ በትናንትናው እለት 745 አዳዲስ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ይህም በሃገሪቷ በአንድ ቀን ብቻ የተመዘገበ ከፍተኛው ቁጥር ሆኗል፡፡

አጠቃላይ በኮቪድ 19 የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 14 ሺህ 229 ደርሷል፡፡

21 ተጨማሪ ሰዎች ትናንት መሞታቸውን የሃገሪቷ ጤና ሚኒስትር አስታውቋል፡፡ይህን ተከትሎም የሟቾች ቁጥር ወደ 680 ከፍ ብሏል፡፡3 ሺህ 994 ሰዎች ደግሞ ከህመማቸው አገግመዋል፡፡

የአለም ጤና ድርጅት ግብጽ የመመርመር አቅሟን ማሳደግ እንዳለባት ቢያሳስብም፤ የጥራት ደረጃው ምን መሆን እንዳለበት ግን ግልጽ አላደረገም፡፡

የሃገሪቷ ባለስልጣናት ለምን ያክል ሰዎች ምርመራ እንደተደረገ መረጃ እየሰጡ አይደለም፡፡ ነገር ግን ፕሬዘዳንቱ አማካሪ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ 105 ሺህ የላቦራቶሪ ምርመራ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በአባይነሽ ሽባባው
ግንቦት 14 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *