ጠቅላይ ሚንስተር ዶክተር አብይ በኢትዮጽያ የተጠለሉ የሶሪያ ስደተኞችን ጎበኙ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ ዛሬ በፌስቡክ ገጻቸው እንዳሰፈሩት የረመዳን ጾም ከማብቃቱ በፊት መልካም የዒድ በዓል እንዲሆንላቸው በመመኘት ዛሬ ሶርያውያን ስደተኞችን ጎብኝቻለሁ።

ሶርያውያኑ አስከፊውን ግጭት በማምለጥ መኖሪያቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉ ሲሆን፣ የረመዳንን ማብቂያ በክብር ማሳለፍ ይገባቸዋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ስደተኞች ከሚቀበሉ ሀገራት መካከል እንደ ሆነች ይታወቃል። ሀገራችን በጦርነት ምክንያት ኑሯቸው ለተናጋባቸው ሰዎች ከለላ ለመስጠት ትሠራለች።

ኢትዮጵያ ከሶሪያ ስደተኞች በተጨማሪ የሶማሊያ፣ኤረትራ፣የመን እና የደቡብ ሱዳን ዜጎችን ያስጠለለች አገር ናት።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ግንቦት 14 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *