የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ለአፍሪካ ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዝደንቱ በላኩት መልዕክት የአፍሪካ ሀገራት ነፃነት ፣ ሰላም እና ብልፅግና ተምሳሌት ለሆነው የአፍሪካ ቀን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

ይህ በዓል የተከበረው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለቅኝ ግዛት ሀገሮችና ህዝቦች ነፃነት ያወጀበት 60 ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል በሚከበርበት ዋዜማ ላይ በመሆኑ ልዩ ትርጉም ያሰጠዋል ብለዋል፡፡

ከበርካታ አሥርት ዓመታት በፊት ብዙ የአፍሪካ ሕዝቦች ወደ ሉዓላዊነት ጎዳና መጓዝ ሲጀምሩ ሀገራችን ሩሲያ ንቁ የፖለቲካ ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ አድርጋለች፡፡

የሰለጠኑ የሲቪል እና ወታደራዊ ሰራተኞች በመላክ አለኝታነቷን አሳይታለች ሲሉም ፕሬዘዳንቱ መናገራቸውን በአዲስ አበባ የሚገኘው የሩሲያ ኢምባሲ አስታውቋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በአለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ በመነጋገር ንቁ ሚና የሚጫወቱ የአፍሪካ ሀገራት የሩሲያ ወሳኝ እና ተስፋ ሰጪ አጋሮች ናቸው ሲሉም አክለዋል፡፡

ባለፈው ዓመት በሱቺ የተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ በሩሲያ እና በአፍሪካ ግንኙነቶች እና ልማት ውስጥ እጅግ ወሳኝ ምዕራፍ የሆነ ነውም ፕሬዝደንት ፑቲን ተናግረዋል፡፡

በሀገራቱ መካከል የተደረገው ምክክር የተሻለ ውጤት ያስገኘ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡

በጉባኤው ወቅት የተቋቋመው የሩሲያ እና የአፍሪካ አጋርነት መድረክ በተለያዩ መስኮች ሁለገብ ጠቃሚ ትብብርን ለመገንባት እና የየአገራችንን አደጋዎች ለማስወገድ የሚደረገውን ጥረት በማስተባበር ጥሩ አጋጣሚ ፈጥሮልናል ብለዋል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል

ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *