የቻይና ኩባንያ ጭምብል ያደረጉ ሰዎችን ማንነት የሚለይ ቴክኖሎጂ ይፋ አደረገ

የቻይና ኩባንያ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ያደረጉ ሰዎች ማንነት መለየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ይፋ አድርጓል።

ቴክኖሎጂው ዓለምን እያስጨነቀ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ለመዋጋት እገዛ እንደሚያደርግ ታምኖበታል።

ሃንቮን በተባለው ኩባንያ የተዋወቀው ቴክኖሎጂ ሰዎችን ጭምብል ሳያወልቁ ማንነታቸውን መለየት የሚያስችል ነው ተብሏል።

በተጨማሪም ከሰውነት ሙቀት መለኪያ መሳሪያዎች ጋር ከተገናኘ በኋላ ከ38 ዲግሪ ሴሊሺየስ በላይ የሰውነት ሙቀት ያላቸውን ሰዎች መለየት እንደሚችል የኩባንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ሁዋንግ ሊ ለሮይተርስ ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈም የወንጀል ተጠርጣሪዎች፣ አሸባሪዎች ወይም የተለያየ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸውን ግለሰቦች መለየት እንደሚችልም ተነግሯል።

ቴክኖሎጂው 30 ያክል ሰወችን በሰከንድ የሚለይ ሲሆን፥ 6 ሚሊየን የሚጠጉ ጭምብል ያደረጉ እና ያላደረጉ ሰወችን ለጥናታቸው መጠቀማቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም ጭምብል ያደረጉ ሰወችን የመለየት አቅሙ 95 በመቶ ሲሆን፥ 99 ነጥብ 5 በመቶ ደግሞ ጭምብል ያላደረጉ ሰዎችን የመለየት አቅም አለው ነው የተባለው።

በአሁኑ ወቅት የኮሮና ቫይረስ ዓለም ላይ መስፋፋቱን ተከትሎ የፊት ጭምብል መጠቀም የግድ ሲሆን ቴክኖሎጂውን ከቻይና በተጨማሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ መጠቀም ጠቀሜታው ከፍ ያለ መሆኑ ተነግሯል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *