በአዲስ አበባ ቦሌ አትላስ አካባቢ ዛሬ ሌሊት በአንድ መኖሪያ ቤት በጦር መሳሪያ እና በኤሌክትሪክ ሾክ የታገዘ ዝርፊያ ተፈጸመ።

በአዲስ አበባ ከኡራኤል ቦሌ አትላስ መስመር አካባቢ በተለምዶ ይልማ ስጋ ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ማለትም ሰኞ ለማክሰኞ ሌሊት ላይ የተደራጁ ዘራፊዎች በአንድ መኖሪያ ቤት ላይ ዝርፊያ መፈጸማቸው ተገልጿል።

ዝርፊያው የተፈጸመበት ግለሰብ አቶ ረብራ ተሸመ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳለው ዘራፊዎቹ በጦር መሳሪያ እና የኤሌክትሪክ ሾክ በመጠቀም 2 ላፕ ቶፕ 2 አይፎን ስልኮች 10 ሺህ 800 ብር በጥሬ ገንዘብ እና የተለያዩ የቤት ንብረቶች ዘርፈው ተሰውረዋል።

አቶ ረብራ እንዳሉን በኤሌክትሪክ ሾኩ በተፈመበት ጥቃትም ለሰዓታት ያህል እራሱን ስቶ እንደነበረ ነግሮናል፡፡ከኤልክትሪክ ሾክ በተጨማሪም በገጀራ አንገቱ አካባቢ ጉዳት እንዳደረሱበትም ተናግሯል፡፡

ዘራፊዎቹ የዘረፉትን ንብረት በያዙት መኪና በመጫን ከአካባው እንደተሰወሩ የተናገሩት አቶ ረብራ የአካባቢው ሰው ሲከተላቸው ተኩስ መክፈታቸውንም ነግሮናል፡፡

አቶ ረብራ ዝርፊያውን አስመልክቶ በአካባቢው ለሚገኘው ካራማራ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ማመልከቱንም ተናግሯል።

ጉዳዩን ለማጣራትም ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም ያልተሳካልን ሲሆን በቀጣይ ፖሊስ የደረሰበትን ሂደት ተከታትለን የምናሳውቅ ይሆናል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *