በፕሪምየር ሊጉ የተጫዋቾች የመጎዳት ዕድል እንደሚጨምር አንድ የጥናት ውጤት አመላከተ::

ፕሪምየር ሊጉ ዳግም ወደ ውድድር ሲመለስ ሊተገበር የታሰበው ተደራራቢ የጨዋታ መርሃግብር የተጫዋቾችን የመጎዳት እድል በ25 በመቶ እንደሚያሳድገው አንድ የጥናት ውጤት አመላክቷል። ።

የፕሪምየር ሊጉ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሪቻርድ ማስተርስ ፕሪምየር ሊጉ ሰኔ ውስጥ እንደሚጀመር “ከመቼውም ጊዜ በላይ እርግጠኞች ነን” ማለታቸው ይታወሳል። የ2020-21 የውድድር ዘመን ጀመጀመሩ በፊት”በነሐሴ መጨረሻ አሊያም በመስከረም መጀመሪያ” የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታዎች የሚከናወኑበት ጊዜ መፈለግ እንደሚኖርበትም ተገልጿል። ፕሪምየር ሊጉ ሊጀመር ይችላል በተባለበት ሰኔ 20 ወደ ውድድር ቢመለስ እንኳን የማንቸስተር ሲቲ ተጫዋቾች በ49 ቀናት ውስጥ 13 ጨዋታዎችን ከማድረግ ይገደዳሉ። ሲቲ ያከናወነው ከአብዛኞቹ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች በአንድ የሚያንስ ጨዋታዎችን ነው። ይህ ቁጥር ግን የሻምፒየንስ ሊግን መጠናቀቅ ከግምት ያላስገባ ነው።

የአውሮፓ መድረክ ውድድር የሚጠናቀቅ ከሆነ እና ሲቲ እስከ ፍጻሜ የሚጓዝ ከሆነ እስከ አራት ተጨማሪ ጨዋታዎችን ሊያከናውን የሚችልበት ዕድል አለ። የጉዳት ተጋላጭነትን በመተንበይ ስፔሻላይዝድ ያደረገው እና በመላው ዓለም ከሚገኙ 35 ፕሮፌሽናል ክለቦች ጋር የሚሰራው ዞን7 የሰራው ጥናት በ30 ቀናት ውስጥ ስምንት ጨዋታዎችን ማከናወን የጉዳትን የመከሰት ዕድል በ25 በመቶ ከፍ እንደሚያደርገው ያመላክታል። በ30 ቀናት ውድጥ ስምንት ጨዋታዎችን ማከናወን የተለመደ ነገር ይመስላል ። ነገር ግን በየውድድር ዘመኑ በዚህ ዓይነት መንገድ እንዲጫወቱ የሚገደዱት 4በመቶ ያህል ተጫዋቾች ብቻ ነበሩ ።

አሳሳቢው ነገር የጨዋታዎች መደራረብ ብቻ አይደለም። ተጫዋቾች በተነጠል ሲሰሩት ከነበረው ልምምድ ወደ ተጋጋለው የቡድን ልምምድ የሚሸጋገሩበት ጊዜ አጭር መሆኑም ጭምር እንጂ። የዋትፎርዱን አሰልጣኝ ናይጀል ፒርሰን እና የኒውካስሉን አሰልጣኝ ስቲቭ ብሩስ ያሳሰባቸውም ይሄው ነው። የኒውካስሉ አሰልጣኝ ስቲቭ ብሩስ “ተጫዋቾች በቂ የመዘጋጃ ጊዜ ካላገኙ እንደ ወረቀት ይረግፋሉ ” ለማለት የተገደዱት ለዙህ ይመስላል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በአቤል ጀቤሳ

ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *