በአዲስ አበባ አራት የግል ትምህርት ቤቶች ለአንድ ዓመት ታገዱ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ጥራት ሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን ዛሬ በሰጠው መግለጫ በአዲስ አበባ አራት ትምህርት ቤቶች በቀጠቀዩ ዓመት ተማሪዎችን ተቀብለው እንዳያስተምሩ ታግደዋል።

ባለሰልጣኑ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የትምህርት ቤት ክፍያቸውን ከ50 እስከ 75 በመቶ እንዲቀንሱ መመሪያ ቢያስተላልፍም ትምህርት ቤቶቹ ግን 100 ፐርሰነት ክፍያ አስከፍለው ነው።

ለአንድ ዓመት ከታገዱት ትምህርት ቤቶች መካከልም 3ኤም ትምህርት ቤት፣ገነት መሰረተ ክርስቶስ፣ሮማን አካዳሚ እና ለምለም ትምህርት ቤቶች በ2013 ዓመት ተማሪ እንዳይቀበሉ ተወስኖባቸዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *