በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቅጥር ከ115 ሺህ ተሻግሯል፡፡

የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማእከል ሲ ዲ ሲ እንዳስታወቀው እስከ ትናንት ከሰዓት ድረስ በአፍሪካ ምድር በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 115 ሺህ 616 ደርሷል፡፡ የሟቾች ቁጥር ደግሞ 3 ሺህ 479 ደርሷል፡፡

በሲ ዲ ሲ ሪፖርት የትናንት መሰረት 46 ሺህ 630 ሰዎች ደግሞ ከኮቪድ-19 አገግመዋል፡፡

ደቡብ አፍሪካ 23 ሺህ 615 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙባት ሲሆን በቀጠናው ቀዳሚዋ ሃገር ሆናለች፡፡ ግብጽ 17 ሺህ 967 ዜጎቿ በቫይረሱ ተይዘውባታል፡፡

አልጄሪያ ደግሞ 8 ሺህ 503 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን አረጋግጣለች፡፡ናይጄሪያ 8ሺህ 63፣ ሞሮኮ 7 ሺህ 556 ዜጎቻቸው በዚሁ ወረርሽኝ ተይዘውባቸዋል፡፡

እነዚህ አምስት ሃገራት አህጉሪቷ ከፍተኛውን የተጠቂዎች ቁጥር ያስመዘገቡ መሆናቸውን ነው ሲ ዲ ሲን ዋቢ አድርጎ ሲጂቲኤን አፍሪካ የዘገበው፡፡

በበሽታው ስርጭትም ይሁን በሟቾች ቁጥር ከቀጠናው የምእራብ አፍሪካ ሃገራት እየተፈተኑ መሆኑን ነው መረጃው የሚያሳየው፡፡

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በ54ቱም የአፍሪካ ሃገራት መዛመቱንም ሲዲሲ አስታውቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በአባይነሽ ሽባባው

ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *