በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ ከ950 በላይ ሰዎች ድንገተኛ አደጋዎች ደርሶባቸዋል።

በአቤት ሆስፒታል የቃጠሎ እና ድንገተኛ ህክምና ክፍል ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳለው በመጋቢት ወር ብቻ 23 ሰዎች በድንገተኛ አደጋ ሕወታቸው አልፏል፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ምክንያት የእንቅስቃሴ ገደብ ቢጣልም ጎን ለጎን የድንገተኛ አደጋዎች የመከላከል ስራ ትኩረት እንደተነፈገውም ተገልጿል።

በአቤት የቃጠሎ እና ድንገተኛ ህክምና ሆስፒታል በመጋቢት እና በሚያዚያ ወር ብቻ ከ950 በላይ ሰዎች ድገተኛ አደጋ ደርሶባቸዋል።ከዚህ አደጋ ውስጥም ከ300 በላይ የመኪና አደጋዎች መሆናቸው ተነግሯል፡፡

በ2012 ዓ.ም በ10 ወራት ውስጥ በአቤት ሆስፒታል ፣ በአጠቃላይ ከ6 ሺህ 600 በላይ የድንገተኛ የአደጋ ህክምና አገልግሎት መሰጠቱን ሆስፒታሉ አስታውቋል።

ከዚህ ውስጥ ደግሞ ከ2 ሺህ 600 በላይ የመኪና አደጋ መሆኑን ሆስፒታሉ ገልጿል፡፡ በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል የኦርቶፔዲስ እና ታራማቶሎጂ ክፍል ሀላፊ የሆኑት ዶክተር ጥላሁን ደስታ የአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ናቸው።

እሳቸው እንደሚሉት የኮሮና ወረርሺኝ ከመጣ ጀምሮ በአማካኝ በየቀኑ ከ7 እስከ 8 የመኪና አደጋ ተጎጂዎች ወደ ሆስፒታላቸው እየመጣ ነው።

ወረርሺኙ በኢትዮጵያ ከተሰተ ጀምሮም ቁጥሩ እየጨመረ መሆኑን ዶክተር ጥላሁን ነግረውናል፡፡የአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊት ዶክተር ሚሊኪያስ ፀሐይ ደግሞ አደጋው ከጊዜ ወደ ጊዜ በጣም እየጨመረ ነው ብለዋል።

በመሆኑ በኮሮና ምክንያት የሚመጣው ጫና እንዳያባብሰው ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል፡፡

ከመኪና አደጋዎች ባለፈ በግንባታ ላይ እና በሞተር ሳይከል የሚደርሱ አደጋዎች አሁንም እንደቀጠሉ ናቸው፣ በመሆኑም ልዩ ትኩረት መደረግ አለበት ብለዋል ዶክተር ጥላሁን፡፡

ዶክተር ሚልኪያስ፣ አደጋ ከደረሰ በኋላ ህክምና ቢሰጥም፣የአደጋ ችግር በህክምና ብቻ አይፈታም፣ ስለዚህ ለአደጋ ከሚያጋልጡ ማንንኛውን እንቅስቃሴ ህብረተሱ እራሱን መጠበቅ አለበት ብለዋል፡፡

በኢትየጵያ የተሽከርካሪ አደጋ በየአመቱ ከአምስት ሺህ በላይ ሰዎችን ሲገድል ከ15 ሺህ በላይ ሰዎችን ደግሞ አካል ጉዳተኛ እንደሚያደርግ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በዳንኤል መላኩ

ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *