በዓለማችን 54 በመቶ የሚሆኑ የተራድኦ ድርጅት ሰራተኞች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከስራቸው መፈናቀላቸው ተገለጸ።

ዴቬክስ የተሰኘው መቀመጫው ቤልጂየም ብራሰልስ ያደረግ ተቋም ከ162 ሀገራት በሚሰሩ 580 መንግስታዊ ባልሆኑ የተራድኦ ሰራተኞች ላይ ጥናት አድርጓል።

ኮሮና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት ላይ እያደረሰ ያለውን ተጽዕኖ አስመልክቶ ይሄ ጥናት ይፋ ሆኗል።ጥናቱ እንዳመለከተው ቫይረሱ በተራድኦ ድርጅቶች ተቀጥረው በሚሰሩ ሰራተኞች ላይ ተጽእኖው ከፍተኛ ነው።

የነዚህ ድርጅቶች ዋነኛ የገንዘብ ምንጭ የነበሩት የአውሮፓ እና አሜሪካ አገራት በኮሮና ቫይረስ ከፉኛ በመመታታቸው ምክንያት እርዳታ በማቆማቸው ነው ተብሏል።

ከነዚህ መላሾች ውስጥ 60 ከመቶ የሚሆኑት በኮሮና ቫይረስ ምክንየት ስራችን እናጣለን የሚል ፍራቻ አንዳላቸው ለዚህ ተቋም ተናግረዋል።

ምላሻቸውን ከሰጡ ሰዎች ውስጥ 39 ከመቶ የሚሆኑት ከአፍሪካ 31 ከመቶ የሚጠጉት ደግሞ ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት እንዲሁም 6 ከመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከሰሜን አሜሪካ እና ከአውሮፓ በሚገኙ ተቋማት የሚሰሩ ናቸው፡፡

በእርዳታ ላይ ጥገኛ የሆኑ የልማት ድርጅቶች በኮሮና ምክንየት ከፍተኛ ኪሳራ እና ውድመት ሊደርስባቸው ይችላል በዋነኝነት ግን በነዚህ ድርጅቶች ተቀጥረው የሚሰሩት ላይ የከፋ እንደሚሆን ጥናቱ አመላክቷል፡፡

ጉዳቱ ግን ከአህጉር አህጉር እጅጉን የተለያየ እንደሆነም ነው ይሄው ጥናት ያመላከተው፡፡ባሁኑ ሰአትም በተለይ በአፍሪካ የሚገኙ ተራድኦ ድርጅቶች ፊታቸውን አደጋ መከላከል ላይ በማድረጋቸው የተነሳ በርካታ ዜጎች ስራ ፈት ሆነው ይገኛሉ ብሏል ጥናቱ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *