በጋምቤላ ክልል ኮሮና ቫይረስ መመርመር ተጀመረ።

ይህ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ማዕከል በቀን 180 የኮሮና ቫይረስ ናሙናዎችን መመርመር እንደሚያስችል የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

በክልሉ ምርመራ መጀመሩ ጊዜንና ወጪን ከመቆጠብ በተጨማሪ በክልሉ በተለያዩ ለይቶ ማቆያዎች ለሚገኙ ዜጎች በቅርበት አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ተመልክቷል፡፡

ከደቡብ ሱዳን በሚገቡ ስደተኞች ከፍተኛ የኮሮና ስጋት ያለበት የጋምቤላ ክልል ኮሮና ቫይረስን መመርመር የሚያስችል የምርመራ ጣቢያ ዛሬ የክልሉ አመራሮች ስራ አስጀምረዋል።

ከዚህ ቀደም ናሙናዎችን ወደ አዲስ አበባ በመላክ ውጤቶችን ይገልፁ የነበረ ሲሆን በክልሉ ምርመራ መጀመሩ ጊዜንና ወጪን ከመቆጠብ በተጨማሪ በክልሉ በተለያዩ ለይቶ ማቆያዎች ለሚገኙ ዜጎች በቅርበት አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ተብሏል።

በጋምቤላ ክልል ስራ የጀመረው የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ማሽን በቀን እስከ 180 ናሙናዎችን የመመርመር አቅም ያለው ሲሆን ምርመራው ከተጀመረ ወዲህ ሰባት ናሙናዎች ተመርምረው ሁሉም ውጤታቸው ነገቲቭ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ከስደተኞች ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችለውን የቫይረሱን ወረርሽኝ ለመመርመር የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት በክልሉ ከሚገኙ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ውይይት በመደረግ ላይ መሆኑም ተገልጽል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በየውልሰው ገዝሙ

ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *