ከቻይና ወደ አዉስትራሊያ ሲጓጓዝ የነበረ 40 ኮንቴነር የቀዶ ሕክምና ማስክ ባህር ላይ ሰጠመ፡፡

የአዉስትራሊያ የባህር ሃይል ደህንነት ሃላፊዎች እንዳሉት፣የህክምና ባለሙያዎች የሚጠቀሙበትና በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀዉ ሰርጅካል ማስክ ከቻይና ኒንጎ ከተማ ወደ አዉስትራሊያ ሜልቦርኔ ነበር ሲጓጓዝ የነበረዉ፡፡

እቃ ጫኝ መርከቧ የሲንጋፖር ሰንደቅ አላማን ስታዉለበልብ እንደነበር የገለጹት ሃላፊዎቹ፣ የተጫነዉ 40 ኮንቴነር ማስክ በአዉስትራሊያ የባህር ዳርቻ ላይ መስጠሙን ተናግረዋል፡፡

አደጋዉ የተፈጠረዉ እስካሁን ባልታወቀ ምክንያት የመርከቧ ሃይል ለጥቂት ደቂቃዎች ተቋርጦ በተፈጠረ ችግር 40 ኮንቲነሮች ወደ ባህሩ መዉደቃቸዉንና ሌሎች 74 ኮንቲነሮች ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡

በዚህም መርከቧ ወደ ሜልቦርን ሳይሆን ወደ ሌላዋ የአዉስትራሊያ ከተማ ብሪስባኔ እንድትጓዝ መደረጉን ሃላፊዎቹ ለፎክስ ኒዉስ ተናግረዋል፡፡

መርከቧ የጫነችዉ የህክምና የግንባታ ቁሳቁሶችን በመሆኑ በኮንቲነሮቹ ግጭት የደረሰዉ አደጋ በአካባቢዉ ላይ የሚፈጥረዉ የጎላ ችግር አለመኖሩን የተናገሩት ሃላፊዎቹ፣ መርከቧ ምን ያህል ኮንቲነሮችን ጭና ጉዞ ላይ እንደነበረች ግን የተገለጸ ነገር የለም፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በሙሉቀን አሰፋ

ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *