ኮቪድ19 ሆፕ ፎር አፍሪካ ኮንሰርት የተሰኘ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ድግስ የፊታችን እሁድ ምሽት ይካሄዳል ተባለ።

መልቲቾይዝ ኢትዮጵያ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ ይህ ኮንሰርት መልቲቾይስ ከዋን አፍሪካ ግሎባል ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን ታላላቅ የአፍሪካ አርቲስቶችና ታዋቂ ግለሰቦች ይሳተፋሉ ብሏል።

ኮንሰርቱ መልቲቾይስ ከዋን አፍሪካ ግሎባል ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በመላው አፍሪካ በዲኤስቲቪ ቻናል 154 የፊታችን እሁድ ግንቦት 23/2012 ከምሽቱ 2 ሰአት ጀምሮ ይተላለፋል ተብሏል።

ይህ ኮንሰርት በመላው አፍሪካ በዲኤስቲቪ Africa Magic Family , Channel 154 ላይ የሚተላለፍ ሲሆን ታላላቅ የአፍሪካ ድምጻዊያንና ታዋቂ ግለሰቦችን ከቤታቸው የሚያሳትፍና ገቢው በመላው አፍሪካ የኮሮና ቫይረስን ከፊት ለፊት ሆነው በመዋጋት ላይ ላሉ የጤና ባለሙያዎች ድጋፍ ለማድረግ የሚውል ነው።

ዋን አፍሪካ ግሎባል ፋውንዴሽን የዋን አፍሪካ ግሎባል የልማት ክንፍ ሲሆን መንግስታዊ ያልሆነና ለትርፍ ያልተቋቋመ ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ማህበራዊ እድገት የሚሰራ ተቋም ነው።

እሁድ ግንቦት 23 ከምሽቱ 3 ሰአት በዲኤስቲቪ ቻናል 154 የሚተላለፈውም ኮቪድ19 ሆፕ ፎር አፍሪካ የተሰኘውም የሙዚቃ ኮንሰርት አፍሪካንና መላው አለማችንን እያመሰ የሚገኘውን የኮሮና ቫይረስ ለማጥፋት ለሚደረገው ጥረት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ነው ተብሏል።

ይህ ለ3 ሰአታት በቀጥታ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ልዩ ኮንሰርት ታዋቂ የአፍሪካ ድምጻዊያንንና የተለያዩ ታዋቂና ተጽኖ ፈጣሪ ግለሰቦችንም ያካትታል።

ይህ በታላላቅ ኮኮቦች የተሞላው ኮንሰርት ታዋቂዎቹን ቱ ባባ ፡ አኮቴ፡ ባንኪ ደብሊው፡ ቤቲ ጂ፡ ልጅ ሚካኤል ፋፍ : ሲአይሲ፡ ኮብሃምስ አሱኮ ፡ ዳኮሬ ኤግቡሰን፡ ዳኮሬ ኤግቡሰን አካንዴ ፡ ዴኖላ ግሬይ፡ ዳያመንድ ፕላትኑምዝ፡ ኤዲ ጄይ፡ ጃፋራህ፣ ጄፍ ማክሲመም ፡ ኪ ቤንዳ ፡ ኦሳል ጎንዳሮ ፡ፕሪንሰስ ጂናፕ ሲሳይ፡ ፕራይዛንዴ ዋጄ እና ሌሎችንም ያከተተ ሲሆን፡ ሁሉም ከቤታቸው ሆነው ለአፍሪካውያን ሁሉ የተስፋና የማበረታቻ መልክቶች ያስተላልፋሉ::

ከዋን አፍሪካ ግሎባል ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ዘ ኮቪድ19 ሆፕ ፎር አፍሪካ የተሰኘውን ኮንሰርት ከሰሃራ በታች ባሉ 49 ሃገራት እንደሚተላለፍ የመልቲቾይስ ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ወ/ሮ ገሊላ ገብረሚካኤል ተናግረዋል።

በዚህ ኮንሰርት የሚገኘው ገቢ በመላው አህጉሪቱ የኮሮና ቫይረስን ከፊት ተጋፍጠው እየተዋጉ ላሉ የጤና ባለሙያዎች ደህንነት መጠበቂያ እንዲውል የሚደረግ ነው።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *