የትላንት የጀርመን ቡንደስሊጋ ውጤቶች

ትላንት የጀርመን ቡንደስሊጋ ቀጥሎ ተከናውኗል።

ቨርደር ብሬመን 0 – 0 ቦሩሲያ ምንቼግላድባክ

አይንትራክት ፍራንክፈርት 3 – 3 ፍሬይቡርግ

ባየር ሉቨርኩዘን 1 – 4 ዎልፍስበርግ

ቦሩሲያ ዶርትሙንድ 0 – 1ባየርን ሙኒክ

ባየርን ሙኒክ የቡንደስሊጋውን ዋንጫ ለስምንተኛ ተከታታይ ጊዜ ለማንሳት እያደረገ ያለውን ጥረት አንድ እርምጃ ያሳደገለትን ውጤት ትላንት ምሽት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ወደተቀመጠው ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ሜዳ በመሄድ አስመዝግቧል።

በጨዋታው የመጀመሪያ ደቂቃዎች ሁለቱም ቡድኖች ወደ ጎል እጅግ የቀረቡባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ ።። ባየርን መሪነቱን የጨበጠው በመጀመሪያው አጋማሽ ጆሹዋ ኪሚች ከ20 ያርድ ርቀት ባስቆጠራት ጎል ነው ። ጎሏ ከፍጹም ቅጣት ምት ሳጥኑ ውጪ ቺፕ የተደረገች ሀሪፍ ጎል ነበረች። ዶርትሙንድ በሁለተኛው አጋማሽ ጄደን ሳንቾን ወደ ሜዳ ቢያስገባም ልዩነት መፍጠር አልቻለም።

ባየርን ጨዋታውን በማሸነፉ ከዶርትሙንድ ጋር የነበረውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሰባት አስፍቷል። ከዚህ በኋላ የሚቀሩት ስድስት ጨዋታዎች ናቸው። በጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ሮበርት ሌቫንዶቭስኪ የባየርንን መሪነት ወደ ሁለት ከፍ የሚያደርግ ጎል ለማስቆጠር እጅግ ተቃርቦ ነበር።

ኳሷ ቋሚውን ታካ ወጣች እንጂ። የጨዋታው መጠናቀቅን የሚያበስረውን ፊሽካ ሲሰሙ የባተርን ረጫዋቾች ደስታቸውን የገለጹበት መንገድ ከዶርትመየንድ የወሰደየት ሶስት ነጥብ ዋጋው ምን ያህል እንደሆነ ያሳየ ነበር። በዋንጫ ፈየክክሩ ላይ የራሱ የሆነ ተጽዕኖ ያሳርፋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በአቤል ጀቤሳ

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *