ጃክ ዊልሼር ስለ አርሰናል ትውስታው ፣ ስለ ባርሴሎናው ጨዋታ እና ሴስክ ፋብሪጋዝ …..

ጃክ ዊልሼር ያለፈው አስር ዓመት ብዙ የተባለለት እንግሊዛዊ ተጫዋች ነበር። አርሰናል ባርሴሎናን 2ለ1 ባሸነፈበት የ2011ዱ ጨዋታ ላይ በመሰለፉ ደስተኛ መሆኑንም ይናገራል። “ጃኩዚ ውስጥ ከዎይቼች ሼዝኒ ጋር ቁጭ ብለን ያወራነውን አስታውሰዋለሁ።

‘ባርሴሎናን አሸነፍን’ ሲለኝ ትዝ ይለኛል። “በዚያ ቡድን ውስጥ ሊዮኔል ሜሲ፣ ዴቪድ ቪያ ፣ ፔድሮ ፣ዣቪ፣ አንድሬስ ኢኒዬሽታ እና ሌሎችም የተካተቱበት ነበር። ከጨዋታው በኋላ ስለ ጃክ ዊልሼር ብዙ ብዙ ነገሮች ተባሉ።” ፔፕ ጓርዲዮላ ግን አረጋጋኝ። በባርሴሎና ቢ ቡድን ውስጥ የእርሱ ዓይነት ብዙ ታዳጊዎች አሉ” አለኝ። በአርሰናል ጥሩ ምክር የሚሰጠው ተጫዋች ፋብሪጋስ እንደነበርም አስታውሷል። “እርሱ ወደ ዋናው ቡድን ሰብሮ ሲገባ 12 ዓመቴ ነበር። የምፈልገው እንደ እርሱ መሆን ነበር።

አሁን ላይ ጥሩ ጓደኞች ሆነናል ። እኔ ወደ ዋናው ቡድን ስቀላቀል ግን እርሱ ኮከብ ሆኖ ነበር” ይላል የ28 ዓመቱ አማካይ። በሮበን ቫን ፔርሲ የማንቸስተር ዩናይትድ ዝውውር ግን መደንገጡን እና ማዘኑን አልሸሸገም። “ቀደም ባለው የውድድር ዘመን 30 ጎሎችን አስቆጥሮ ነበር። አምበላችን ነበር። ዳግም ለዋንጫ እንደምንፎካከር አስቤ ነበር። በድንገት ግን ለዋነኛው ተቀናቃኛችን ፈርሞ አረፈው” በማለት አጋጣሚውን በቁጭት ያስታውሳል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በአቤል ጀቤሳ

ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *