በኢትዮጵያ ተጨማሪ 30 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,352 የላብራቶሪ ምርመራ ሰላሳ (30) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሰባት መቶ ሰላሳ አንድ (731) ደርሷል፡፡

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው – 11

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው – 5

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው – 14

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አስራ አራት (14) ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን ይህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሰማንያ አንድ (181) ደርሷል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓ.ም


FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *