19 ዶክተሮቿን ኮሮና የገደለባት ግብጽ በሐኪሞቿ አሟሟት ዙሪያ ምርመራ እንዲደረግ አዘዘች፡፡

የግብጽ የጤና ሚኒስትር መርመራው እንዲደረግ የወሰነው ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የህክምና ሰዎች ሞት በመጨመሩ ነው፡፡ሚኒስትር ሃላ ዛይድ በዶክተር ዋሊድ ይሄያ ሞት ጋር በተገናኘ የነበረ ቸልተኝነት ያለ እንደሆነ ምርመራ እንዲደረግ ወስኗል፡፡

የግብጽ መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት ይህ ትዕዛዝ የወረደው ቀጥታ ከፕሬዝደንት አብዱል ፋታህ አልሲሲሰ ነው፡፡

ይህ የሆነው የዶክተሮች ህብረት በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ቸልተኛነት ላይ ክስ መመስረቱና የኮሮና ቫይረስ ለ19 ዶክተሮች ሞት ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ማድረጉን ተከትሎ እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል

ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *